Skip to content

Visit us any time.

የዐማራ ትግል የጋራ ምክርቤት (JCAS)

የዐማራ ትግል የጋራ ምክርቤት (JCAS)

Amharas united will survive and thrive!

  • Who We Are?
  • JCAS Objective
  • Press Releases
  • Latest Posts
  • Contact US
  • Who We Are?
  • JCAS Objective
  • Press Releases
  • Latest Posts
  • Contact US

በሰሜን ሸዋ ዞን ታግተው ከነበሩት 52 መንገደኞች ስምንቱ አሁንም አልተለቀቁም

  1. Home   »  
  2. በሰሜን ሸዋ ዞን ታግተው ከነበሩት 52 መንገደኞች ስምንቱ አሁንም አልተለቀቁም

በሰሜን ሸዋ ዞን ታግተው ከነበሩት 52 መንገደኞች ስምንቱ አሁንም አልተለቀቁም

July 23, 2024September 2, 2024 adminUncategorized

VOA (Sep. 3, 2024)

ትላንት ኀሙስ፣ ከዐዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ በሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ሲጓዙ የነበሩ 52 ሰዎች፣ በታጣቂዎች ታግተው እንደነበር የገለጸው በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር፣ ኾኖም አብዛኛዎቹ ወዲያውኑ አምልጠው ስምንት ተሳፋሪዎች ብቻ መቅረታቸውን አስታውቋል።።

በኦሮሚያ ክልል፣ በገብረ ጉራቻ እና ቱሉ ሚልኪ ከተሞች መካከል ባለ ቦታ ላይ፣ ከማሽላ ማሳ ውስጥ የወጡ ታጣቂዎች አውቶብሱን አስቁመው፣ አሽከርካሪውን ጨምሮ 52 ተሳፋሪዎችን ወደ ጫካ ወስደው እንደነበር ከእገታ ያመለጡ እማኞች ገልጸዋል።

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደሪ አቶ ከፍያለው አደሬ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ 52ቱ ተሳፋሪዎች፣ እርሳቸው “ሸኔ” ሲሉ በገለጹት ታጣቂ ቡድን ታግተው የነበሩ ቢኾንም፣ “የጸጥታ ኀይሎች ብዙዎቹን ማስለቀቅ ችለዋል፤” ብለዋል።

የቀሩትን ስምንት ተሳፋሪዎች ለማስለቀቅም “ጥረቱ ቀጥሏል” ሲሉ ተናግረዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ባልደረቦች፣ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ምላሽ ለማግኘትና በዘገባው ለማካተት ጥረት አድርገዋል፤ ለጊዜው አልተሳካም።

ኾኖም ድርጅቱ፣ ከዚኽ ቀደም ለቀረቡበት መሰል ውንጀላዎች በሰጠው ምላሽ፣ ታጣቂዎቹ በእገታ ተግባራት ላይ እንደማይሳተፉ በመግለጽ በጽኑ አስተባብሏል።

Post navigation

Next: ግጭት የወለደው ቀውስ በአማራ ክልል

One thought on “በሰሜን ሸዋ ዞን ታግተው ከነበሩት 52 መንገደኞች ስምንቱ አሁንም አልተለቀቁም”

  1. A WordPress Commenter says:
    June 15, 2019 at 3:59 am

    Hi, this is a comment.
    To get started with moderating, editing, and deleting comments, please visit the Comments screen in the dashboard.
    Commenter avatars come from Gravatar.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Who we are

Recent Posts

  • ግጭት የወለደው ቀውስ በአማራ ክልል
  • በሰሜን ሸዋ ዞን ታግተው ከነበሩት 52 መንገደኞች ስምንቱ አሁንም አልተለቀቁም

Recent Comments

  • A WordPress Commenter on በሰሜን ሸዋ ዞን ታግተው ከነበሩት 52 መንገደኞች ስምንቱ አሁንም አልተለቀቁም

Archives

  • September 2024
  • July 2024

Categories

  • Uncategorized

Meta

  • Log in
  • Entries feed
  • Comments feed
  • WordPress.org
Proudly powered by WordPress | Theme: goldy-mex by inverstheme.