የምክር ቤቱ የሥራ ክፍሎች

JCAS has many working committees and three of them are listed below.

የሕዝብ ግንኙነት

The Last of us

የምክር ቤቱን ፕሮግራምና ዓላማዎች በልዩ ልዩ መንገዶች ለሕዝብ እንዲዳረስና እዲሰርጽ ያደርጋል፤ በህልውና ትግሉ በህዝባዊ ተሳትፎ እንዲደገፍ ያስተምራል፤ ወገናችን የመደራጀትን አስፈላጊነት አውቆ ወገናችን ምክርቤቱን እንዲቀላቀል ወይም እንዲደግፍ ይቀሰቅሳል፤ ዐማራው ያሉትን እሴቶችና ሁለንተናዊ እውነታዎች የማሳውቅ ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል።

የድርጅት ክፍል

The Last of us

የምክርቤቱን ስራ በሚያግዝ መልኩ የተለያዩ የዐማራ ድርጅቶችንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በአንድነትና በጋራ በመሰባሰብ ብሎም በመተባበር የሕልውናውን ትግል በጋራ እንዲያጠናክሩ ስልቶችን ይቀይሳል፣ መልካምና ጤናማ ግንኙነቶችን ይዘረጋል፣ ግብዐታቸውንም ይከታተላል፣ ተያያዥ ጥናቶችንም ያካሂዳል፣

የሀብት ማሰባሰብና ሎጂስቲክ ክፍል

The Last of us

ምክርቤቱ ለሚዘረጋቸው ፕሮጀክቶች ማስፈጸምያ፣ የአማራውን ህልውና ትግል የሚያግዙ ተቋሞች እገዛ፣ አማራው ተናቦ የህዝባዊ ትግሉ ጠንካራ ተሳታፊ እንዲሆን የቅስቀሳና ልዩ ፕሮግራሞችን እውን ለማድረግ የሚያበቃ የገንዘብ ማሰባሰብ ያደርጋል።

የውጭ ግንኙነት ክፍል

The Last of us

የውጭ ግንኙነት ክፍል ብዙ ኃላፊነቶች ያካተተ ሲሆን ዋንኛው ኝ ከተለያዩ መንግስታት፣ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የምክርቤቱን ዓላማ ማስተዋወቅና በዐማራው ላይ የሚደርስበትን የዘር ማጥፋት ውንጀልና የታወጀበትን ኢፍትሐዊ የሆነ ጦርነት በግልፅ እንዲያውቁት ጥረቶችን ያደርጋል፣ ድጋፍንም ያሰባስባል።

የሀብት ማሰባስባና ሎጂስቲክ ክፍል

The Last of us

ለምክር ቤቱም ሆነ በምድር ላይ ላሉት የትግልና የሥራ እንቅስቃሴዎች ግብአት ሊውሉ የሚችሉ የገንዘብ ርዳታዎች ማሰባሰቢያ ዕቅዶችና ሊረዱ ወይም ሊጠቅሙ ይችላሉ የሚላቸውን ንድፈ ሃሳቦች ይቀርጻል፤ የተለያዩ ንኡስ ኮሚታዎችን አቋቁሞ ያስፈጽማል።

የፖለቲካ ጉዳይ ክፍል

The Last of us

የፖለቲካ ክፍል ዋነኛ ሥራው በመሬት ላይ መፈጠርና መመስረት የሚገባውን የፖለቲካ አደረጃጀት በማንኛውም አስፈላጊ በሆኑ ግዳዮች ላይ ርዳታ መስጠት እና መሳተፍ ነው።

የህልውና ትግል ክፍል

The Last of us

የህልውና ትግል ክፍል ብዙ የኃላፊነት ዘርፎች ያሉት ሲሆን ዋንኛው ግን ሁሉንም የዐማራ አካባቢዎችን ባማከለ መልኩ በመሬት ላይ ካሉ የትግሉ መሪዎች ጋር አብሮ በመስራት ያሉትን አደረጃጀቶች በአንድ ማእከላዊ ተቋም ስር እንዲካተቱ መጣርና ለዚህም ተፈፃሚነት የተለያዩ መንገዶችን በመትለሙ ላይ እገዛ ማድረግ ነው።

የጥናትና ምርምር ክፍል

The Last of us

ምክር ቤቱ ሊመራበት የሚገባቸውን ፖሊሲዎችን ያጠናል፤ የዐማራውን ዘርፈ በዙ ችግሮች ያጠናል ይመረምራል፤ የመፍትሔ ሀሳቦችንም ያፈልቃል፤ ተግባራዊም የሚሆኑበትን መንገድ ያዘጋጃል።

የመረጃ አሰባሳቢና ትንታኔ ክፍል

The Last of us

ይህ ክፍል ብዙ ኃላፊነቶች ያሉት ሲሆን በዋነኛነት ለመረጃ ሥራ ውጤታማነትና ለቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ የሚያመች የአመራርና የአሠራር ግንኙነት ዘዴ ያጠናል፤ ተግባራዊም ያደርጋል፤

የአቅም ግንባታ ክፍል

The Last of us

ይህ ክፍል ብዙ ኃላፊነቶችን ያሉት ሲሆን አንዱና ዋናው ከአባላት መካከል ሥልጠና ወይም ትምህርት ቢሰጣቸው ለምክር ቤቱ ብሎም ለሕልውናው ትግል ጥንካሬ ያግዛሉ የሚባሉትን እያጠና እንዲሰለጥኑ ወይም እንዲማሩ ያደርጋል፤ እንዳስፈላጊነቱ የህልውና ትግል አመራሮችና አባላት የአመራር ክህሎትን ማዳበር እንዲቻል በልክ የተቀመሩ ስልጠናዎችን ያዘጋጃል።

የመረጃ ቴክኖሎጂ ክፍል

The Last of us

ይህ ክፍል የምክርቤቱ አባላት አመራርና አባላት፣ የህልውና ትግል ተሳታፊዎች፣ እንዲሁም የዐማራ አንቂዎች እራሳቸውንና ትግሉን በሚጠብቅ መልኩ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ የሚያስችል በጥናት ላይ የተመሰረት መፍትሄዎችን ያዘጋጃል፤ ለተጠቃሚዎችም ስልጠናና ምክር ይሰጣል።